ለተፈጥሮ ሰዎች ብቻ ሳይሆን በህግ ሰውነት ላገኙም የፍትህ ብርሀን ነን ስንል በምክንያት ነው!

ከሳሽ፡-የኢትዮጵያ ማየት እና መስማት  የተሳናቸው ብሔራዊ  ማህበር

ተከሳሽ፡- ጋርድያን ሴኩሪቲ ኤንድ ጀነራል ሰርቪስ  

መዝገብ ቁጥር፡– 190836

በ2014 የክረምት ወራት የኢትዮጵያ ማየት እና መስማት  የተሳናቸው ብሔራዊ  ማህበር ንብረት በጥበቃነት ተቀጥረው በሚያገለግሉ ሰዎች ዝርፊያ የተፈጸመበት የመሆኑ ነገር በፖሊስ ፕሮግራሞች ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች አጋፋሪነት ዜና ሖኖ ወደ ጆሯችሁ መግባቱን እንገምታለን። ጉዳዩ ወደማህበራችን ከመጣ ጀምሮም የተበዳይን ጥቅም ባስጠበቀ መንገድ እንዲቋጭ ስንተጋ ቆይተናል። ይሁን እና ባለጉዳዮቹን በቢሯችን ውስጥ ለማስማማት አለመቻሉን ተከትሎ፤ ብሄራዊ ማህበሩን ወክለን ወደፍርድቤት ጎራ ብለን ነበር፤ የፍርድቤቱን ደጅ ከረገጥን በኋላ ግን ሁለቱም ወገኖች ጉዳዩን በስምምነት ለመቋጨት  በመስማማት እና ተከሳሽ ጋርድያን ሴኩሪቲ ኤንድ ጀነራል ሰርቪስ  ለኢትዮጵያ ማየት እና  መስማት ለተሳናቸው ብሔራዊ  ማህበር አራት መቶሽህ ብር ለመክፈል በመስማማቱ ጉዳዩ በስምምነት ተጠናቋል። በዚህ ሰአትም ማህበሩ ሶስት መቶ ሀምሳሽህ ብሩን የተቀበለ ሲሆን ቀሪውን ሐምሳሺሕ ብር  ደግሞ እስከ ጥር ሰላሳ ድረስ ከተከሳሽ  የሚከፈለው ይሆናል ዝርዝሩን ከዚህ መዝገብ ማንበብ ይቻላል።

Skip to content